ለውጥ ከየት ይጀምራል?
****************
ለውጥ ሂደት እንደመሆኑ መጠን ሂደት ደግሞ ጅማሮ ይኖረዋል ፤ የአንድን ነገር ቀድሞ የነበረ ሁኔታ፣ባህርይ፣ መልክ፣… በሌላ እንዲቀየር ወይም እንዲተካ ማድረግ ሲያስፈልግ በመጀመሪያ ወደ እዝነ-ልቦናችን (conscious mind በእንግሊዝ አፍ መጣሁባቹ….:D) የሚመጣብን ነገር ለውጥ ከየት ይጀምራል የሚለው ጥያቄ መሆን ይኖርበታል።
“ማሰብ” የለውጥ ሁሉ መነሻ ነው ለ“ማሰብ” ደግሞ መኖር ያስፈልጋል (ስለመኖራቹ እንዳትጠራጠሩ…..:P) የራስን መኖር በትምህርት የሚረጋገጥ ወይም ሌሎች የሚያረጋግጡልን ሳይሆን በቀጥታ በራሳችን ምስክርነት የሚረጋገጥ ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን ፤የአስራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን ታዋቂው ፈረንሳዊ ፈላስፋ የዲካርት የታወቀች ንግርት እዚህ ላይ ማንሳት ጠቃሚ ይሆናል… “I think; therefore I am” ተመጣጣኝ ትርጉሙ “ስለማስብ ስለዚህ አለሁ” ይላል……አንድ ሰው መኖሩን የሚጠራጠር ከሆነ ለዚሁ ለጥርጣሪውም ቢሆን መኖር መቻሉ የግድ ይለዋል።ስለዚህ የራሱን መኖር የሚጠራጠር ሰው ቢያንስ ለመጠራጠር መኖር ስለሚኖርበት የራስን መኖር ለማወቅ ከራሳችን ውጭ በቀዳሚነት አሳማኝ ማን ሊመጣ? ስለዚህ የለውጥ መነሻ ሊሆን የሚገባው ለመለወጥ(“ለ”ጠብቃ ትነበባለች) ማሰብ መጀመር ነው።።(ሰምንት ነጥብ…..:D)

No comments:
Post a Comment