Monday, August 25, 2014

“Ice Bucket Challenge” እና ኢትዮጵያዊነት

“Ice Bucket Challenge” እና ኢትዮጵያዊነት
ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እየጠፋብን ይመስላል እደዚህ ለማለት የተገደድኩት ጨለምተኛ ወይም ፈራጅ አስተሳሰብ ኖሮኝ ሳይሆን የሰሞኑ “Ice Bucket Challenge” እንቅስቃሴ አንድ ባልዲ ውሃ ለኛ ለኢትዮጲያውያን ምን ያክል አስፈላጊ እንደሆነ ባለመረዳት ወይም ፈረንጅ ያደረገው አይቅርብን በማለት ብቻ ኢትዮጵያውያን ሲሳተፉ በማየቴ ነው
ኢትዮጵያዊነት ባገኘው ነፋስ ወደተፈለገው ቦታ የሚነዳ ማንነት አይደለም ደግሞ እንኳን ምንደፋው የምንጠጣውም ውሃ በቅጡ መች አግኝተን አንድ ባልዲ ውሃ የምናባክነው እንደው ይሁንና መድፋትስ ካለብን የት ይሁን ምን ይሁን ለማናውቀዉ እንቅስቃሴ / ድርጅት ማፍሰሳችን

ኢትዮጵያዊነት ምንም እንበለው ምንም ቁርኝቱ ከኢትዮጲያ ጋርም አይደል እና በጋራ እንጩህ ከተባለ ከALS Association የበለጠ የሀገራችን ወይም  ሀገራዊ ጉዳይ ሳይኖረን ቀርቶ ነው....... ወይ “Ice Bucket Challenge”  

Monday, August 18, 2014

____ ለራስ የሚነገር መልዕክት ___

____ ለራስ የሚነገር መልዕክት ___
እራስክን ከማንማ ጋር አታወዳድር፡፡ ይህን ባደረክ ጊዜ እራስክን በራስህ እንደሰደብክ ቁጠረው፡፡
#መልዕክት 2
ቁልፍን ያለመክፈቻ ማንም እንደማይሰራ ሁሉ ፈጣሪም መፍትሄ የሌለው ችግር እንዲገጥምነ አይፈቅድም፡፡
#መልዕክት 3
ደስታህነ ከራስህ ባራቅህ ጊዜ ሕይዎት በአንተ ላይ ትስቃለች፡፡ ደስተኛ በሆንክ ጊዜ ሕይዎት ፈገግታዋን ትለግስሃለች፡፡ ሌሎች እንዲደሰቱ ምክንያት በሆንክ ጊዜ ግን ሕይዎት የከበረ ሠላምታዋል ታቀርብልሃለች፡፡
#መልዕክት 4
ማንኛውም ስኬታማ ሰው ከበስተጀርባው አስቸጋሪ ታሪኮች እንዳሉት ሁሉ ማንኛውም የችግር(አስቸጋሪ) ታሪክ መጠናቀቂያው ስኬት ይሆናል፡፡ ስለሆነም ችግሩን ተቀበልና ለስኬት ተዘጋጅ፡፡
#መልዕክት 5
የሌሎችን ስህተት ለመተቸት በጣም ቀላል ነው፡፡ ከባዱ ነገር የእራስን ስህተት መረዳቱ ላይ ነው፡፡
#መልዕክት 6
የተፈጠረልህ መልካም አጋጣሚ ባመለጠህ ጊዜ እዛው ባለህበት ቁመህ አይንህን በእንባ አትሙላ፡፡ ቀጣዩንና የተሻለውን መልካም አጋጣሚ እንዳታይ ይከልልሃልና፡፡
#መልዕክት 7
ለችግር ፊትን ማዞር ችግሩን አይቀይረውም ችግሩን መጋፈጥ እንጅ፡፡ በሌሎች ቅሬታን ከማሰማት እራስን ለውጦ ሠላምን መግዛት፡፡
#መልዕክት 8
ስህተት ስህተቱ በተፈተረበት ወቅት ስሜትን ይጎዳል፡፡ ከዓመታት በኋላ የስህተቶች ድምር የሚፈጥረውና ወደ ስኬት የሚያመራው ከስህተት መማር ተሞክሮ(ልምድ) እንለዋለን፡፡
#መልዕክት 9
የቀለጠ ወርቅ ጌጣጌጥ እንደሚሆነው፣
የተጠረበ ድንጋይ ሀውልት እንደሚሆነው ሁሉ፣
አንተም በብዙ ችግር ባለፍክ ቁጥር አንተነትህ እያደገ መሆኑን አትርሳ፡፡ በመሆኑም ስትሸነፍ ጠንካራ ስታሸንፍ የተረጋጋ ሁን፡፡
‪#‎From‬ Personal Development.
(‪#‎ምሥጋናው‬ ግሸን ወልደ አገሬ)
09-12-2006 ዓ.ም

Wednesday, August 13, 2014

ወጣት የነብር ጣት

ወጣት የነብር ጣት
*************
ወጣት መሆን አንዱ የዕድሜ ዕድል ነው። በአስማት ካልሆነ ይህንን እድሜ Escapeን በመጫን መዝለል ወይም መሸወድ አይቻልም። ነብር በጥፍሮቹ የያዘውን ግድ ካልሆነበት እንደማይለቅ ወጣትም እንዲሁ ነው፤ የያዘውን ላለመልቀቅ የሚታገል እና ሊይዘው የሚፈልገው ነገር ሁሉ ትክክል መስሎ የሚታይበት የዕድሜ ክልል መሆኑን ለማስረዳት ምሳሌ መደርደር አያሻም አንድ የምንቀርበውን ወጣት መውሰድ ብቻ በቂ ነው። ።(ስምንት ነጥብ)

Tuesday, August 12, 2014

አሁን ባለንበት ማሕበረሰብ ወጣቶች እያጋጠማቸው ያለ ችግር እና ለውጥ
*********************************************
ወጣቶች በአብዛኛው እያጋጠማቸው ያለው ችግር በዘር፣በሀይማኖት፣….እና በተለያየ መደቦች የተከፋፈለ አይደለም ሁሉም በአንድነት ተመሳሳይ ችግር ከማሕረሰቡ እየደረሰባቸው ነው(ለዘህ ደግሞ ማስረጃ ማጣቀስ አስፈላጊ አይሆንም)።ስለ ወጣቶች ስንነጋገር በብዙ ቦታ እና ብዙ ጊዜ ውይይቶቻችን የሚያተኩሩት ስለ አደገኛ ሱስ(Drug Abuse)፤ስለ ወንጀል(Crime)፤ ስለ ሁከት ወይም ብጥብጥ(Violence)፤ስለ ጽዖታዊ ግኑኝነት፤ ስለ ድዕነት(«ዕ»ጠብቃ ትነበባለች)እና ስለመሳሰሉት ነው፤ እነዚህ ችግሮች የሌሎች ችግሮች ውጤት ናቸው፡፡ከላይ የተጠቀሱ ውጤቶች በአብዛኛው የሚመጡት የሚከተሉትን መሰረት በማድረግ ነው….
፩. የማንነተ ቀውስ(An Identity Crisis)….እኔ ማን ነኝ?
፪. በራስ መተማመን ማጣት እና ስለራስ የተሳሳተ ግምት…..እኔ አልረባም
፫. ተስፋ ማጣት…..እኔ ወዴት ነው የምሄደው?
፬. ግራ መጋባት እና አሻሚ በሆኑ ሐሳቦች መሀል መዋለል…..የትኛው ልክ ወይም ስህተት?
፭. የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ (Electronic Media)አሉታዊ ተጽኖኦች…..እና የመሳሰሉት ናቸው
ስለዚህም ሁላችንም ከወጣቶች ጋር በተያያዘ ከባድ ችግር ፊታችን ላይ እንዳለ ልንረዳ ይገባናል አዳጊ ወጣቶች እና ወጣቶች የወደፊት ጎልማሶች (ሀገር ተረካቢ) እንደመሆናቸው መጠን የተለየ እንክብካቢ ያሻቸዋል ።ሁላችንም አብረናቸው ፣ከጎናቸው በመሆን ይህንን መሰረታዊ ችግር እንዲያለፉት እናግዛቸው።።(ሰምንት ነጥብ)

ዓላማ እና ለውጥ

ዓላማ እና ለውጥ
***********
ዓላማ የሌለው ሰው ተኩሶ አይስትም!!!!ምን ማለት ነው? ዓላማ የሌለው ሰው ወደ'ፊትም ወደ'ኃላም ወደ'የትም አቅጣጫ ቢተኩስ መምታት የሚፈልገው ዒላማ ስለሌለው ተኩሶ የመታውን ቢመታ መታ እንጂ ሳተ ማለት አይቻልም። ዓላማ ያለው ሰው ግን ዓላማውን ለመምታት በሚያደርገው ሙክራ ዒላማውን ሊስት ይችላል ስለ ለውጥ የሚያስብ ደግሞ አንዴ፣ሁለቴ......መቶ ጊዜ ቢስት እራሱን እያሻሻለ እና እየለወጠ ዓላማው ጋር እስኪደርስ ወይም ዒላማውን እስኪመታ ተስፋ አይቆርጥም።።(ስምንት ነጥብ)

Thursday, August 7, 2014

ለውጥ እና ነውጥ

ለውጥ እና ነውጥ
***********
ለውጥ እና ነውጥ አብዛኛውን አብረው እንደ ሚጓዙ፤ በተለምዶም ቢሆን “ለውጥ ነውጥን ይፈጥራል” እንደሚባል ለዚህም ደግሞ አብዛኞቻችን ምሰክር መሆን እንችላለን….. ለለውጥ ተብሎ ቤተሰብ፣አካባቢ፣ህብረ-ተሰብ፣ሀገር ሲናወጥ አይተናል ወይም ሰምተናል …. ነውጡ ያመጣው ለውጥ አዎንታዊ ይሁን አሉታዊ ነውጡን ግን የሚፈጥረው የለውጥ ፍላጎት ነው።
እራሱን መለወጥ የሚፈልግ መናወጡ ከራሱ ይጀምራል፤ አካባቢን፣ቀበሌን(…ቀበሌ ከቀረ ቆየ”ወረዳ”ሆነ…)፣ሀገርን…..ወ.ዘ.ተ. ለመለወጥ የሚነሳ ነውጡ በከፍተኛ ሁኔታ ብዙ ቦታ ሊያካልል ይችላል በዚህ ግዜ ነውጥ ዋጋ የሚያስከፍል የለውጥ አንዱ አካል ይሆናል ዋጋ መክፈል ያለብን ደግሞ ዋጋ መከፈል ላለበት ነገር ብቻ መሆን አለበት …..ለ”በስማ በለው” እና ለ“ላም አለኝ….” አይነቶቹ ለውጥ ዋጋ መክፈል አዋጭ አይደልም።
ስለዚህ ነውጥን አትፍሩት ምክንያቱም ለውጡ የሚፈጥረው ሊሆን ስለሚችል።።(ስምንት ነጥብ)